Shareholder Notice · የባለአክሲዮኖች ማስታወቂያ

General Assembly.

6th Ordinary & 4th Extraordinary Session
Tikimt 24, 2019 E.C. · 3 November 2026
All announcements
የኒኦ አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም አ.ማ
የባለአክሲዮኖች 6ኛ መደበኛ እና 4ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ
የጉባኤ ጥሪ

በኢትዮጵያ የንግድ ሕግ አዋጅ ቁጥር 1243/2013 አንቀጽ 366 (1)፤ 367 (1)፤ 370 እና 393 እንዲሁም በተቋሙ መመስረቻ ጽሑፍ አንቀጽ አስራ ስምንት (1) መሰረት የኒኦ አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም አ.ማ የባለአክሲዮኖች 6ኛ መደበኛ እና አራተኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ የሚከተለውን ጊዜ በኢሊሊ ሆቴል የመሰብሰቢያ አዳራሽ ውስጥ ያካሂዳል፡፡ በመሆኑም የተከበራችሁ የተቋሙ ባለአክሲዮኖች በዕለቱ በጉባኤው ላይ እንድትገኙልን የተቋሙ የዳይሬክተሮች ቦርድ በአክብሮት ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡

ማክሰኞ ጥቅምት 24 ቀን 2019 ዓ.ም · ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ጀምሮ · ኢሊሊ ሆቴል
Tuesday, Tikimt 24, 2019 E.C. (3 November 2026) · from 9:00 AM · Elilly International Hotel, meeting hall
1. አክሲዮን ማህበሩን የሚመለከቱ ዋና ዋና መረጃዎች
ዋና መ/ቤት አድራሻ · Head office
አዲስ አበባ · ቂርቆስ ክ/ከተማ · ወረዳ 8 · ንጉስት ታወር
ድህረ ገጽ · Website
neo.et
የምዝገባ ቁጥር · Registration No.
MT/AA/3/0053054/2014
የማህበሩ ስም · Company name
ኒኦ አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም አ.ማ
የማህበሩ አይነት · Type
በማይክሮፋይናንስ ስራ የተሰማራ
የተፈረመ ካፒታል · Subscribed capital
ብር 200,000,000.00
የተከፈለ ካፒታል · Paid-up capital
ብር 200,000,000.00
2. የ6ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ አጀንዳዎች
  1. የጉባኤውን አጀንዳዎች ማጽደቅ፤
  2. እ.ኤ.አ የ2025/26 ዓመታዊ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሪፖርት ማዳመጥ እና በቀረበው ሪፖርት ላይ ተወያይቶ ማጽደቅ፤
  3. እ.ኤ.አ የ2025/2026 ዓመታዊ የውጭ ኦዲተሮች ሪፖርት ማዳመጥ እና በቀረበው ሪፖርት ላይ ተወያይቶ ማጽደቅ፤
  4. በማህበሩ ከተፈረሙ አክሲዮኖች መካከል በ2025/2026 በጀት ዓመት መከፈል ያለባቸው ለነባር ባለአክሲዮኖች የተከፋፈሉ አዳዲስ አክሲዮኖች ሙሉ በሙሉ በጥሬ ገንዘብ መከፈላቸውን ሪፖርት መስማት እና ተወያይቶ መወሰን፤
  5. በ2025/2026 በጀት ዓመት በተገኘው የተጣራ ትርፍ አደላደል እና አከፋፈል ላይ ተወያይቶ መወሰን፤
  6. ከዲጂታል ዘርፍ (Fair Cash) ከሚገኘው የተጣራ ትርፍ የተቋሙን ድርሻ (60%) ለቀጣይ አምስት ዓመታት ለባለአክሲዮኖች ሳይከፋፈል ለተቋሙ ካፒታል ማሳደጊያ እንዲውል ተወያይቶ መወሰን፤
  7. ለዳይሬክተሮች ቦርድ የሚከፈለውን አበል/ክፍያ ላይ ተወያይቶ መወሰን፤
  8. የጉባኤውን ቃለ ጉባኤ ማጽደቅ፡፡
3. የ4ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ አጀንዳዎች
  1. የጉባኤውን አጀንዳዎች ማጽደቅ፤
  2. የማህበሩን መመስረቻ ጽሑፍ ማሻሻል፤
  3. የተቋሙን የካፒታል እድገት በተመለከተ ተወያይቶ መወሰን፤
  4. የጉባኤውን ቃለ ጉባኤ ማጽደቅ፡፡
4. ማሳሰቢያ
  1. ባለአክሲዮኖች ለስብሰባ በሚመጡበት ጊዜ ማንነትን የሚያረጋግጥ የታደሰ የቀበሌ የነዋሪነት መታወቂያ፤ የፋይዳ መታወቂያ፤ ፓስፖርት ወይንም መንጃ ፍቃድ — ዋናውን እና ቅጂውን ይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል፤
  2. በጉባኤው ላይ በአካል የማይገኙ ባለአክሲዮኖች በንግድ ሕግ አንቀጽ 373 መሰረት በወኪሎቻቸው አማካይነት መሳተፍ የሚችሉ ሲሆን፤ ውል ለማዋዋል ስልጣን በተሰጠው አካል የተረጋገጠ የውክልና ማስረጃ በመያዝ በተወካይ አማካይነት በጉባኤው ላይ መሳተፍ ይችላሉ፤
  3. በባለአክሲዮኖች የተሰጠ ወይም ውል ለማዋዋል ስልጣን በተሰጠው አካል የተረጋገጠ ማስረጃ የያዛችሁ ተወካዮች፤
    1. የወኪሉን የታደሰ የቀበሌ መታወቂያ፤ የፋይዳ መታወቂያ፤ ፓስፖርት ወይም መንጃ ፍቃድ ቅጂ እንዲሁም፤
    2. በጉባኤው ለመሳተፍ እና ድምጽ ለመስጠት የሚያስችል የውክልና ስልጣን ማስረጃ — ዋናውን እና ቅጂውን ይዛችሁ በመቅረብ በጉባኤው ላይ መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን በአክብሮት እናሳውቃለን፡፡
ኒኦ አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም አ.ማ
የዳይሬክተሮች ቦርድ

In brief (English): The Board of Directors of Neo Microfinance Institution S.C. convenes the 6th Ordinary and 4th Extraordinary General Assembly of Shareholders on Tuesday, Tikimt 24, 2019 E.C. (3 November 2026) from 9:00 AM at the Elilly International Hotel meeting hall, under Commercial Code Proclamation No. 1243/2013. Ordinary agenda: adopt the agenda; receive and approve the FY 2025/26 Board of Directors’ report and the external auditors’ report; receive and decide on the report that new shares allotted to existing shareholders for FY 2025/26 were paid in full in cash; decide on the allocation and distribution of FY 2025/26 net profit; decide on retaining the Institution’s 60% share of net profit from the digital segment (Fair Cash) for the next five years as capital growth rather than distributing it; decide on Board remuneration; approve the minutes. Extraordinary agenda: adopt the agenda; amend the Memorandum of Association; decide on the Institution’s capital increase; approve the minutes. Attending shareholders must bring the original and a copy of a valid ID (Kebele residence ID, Fayda, passport, or driving licence); proxies may attend under Article 373 with an authenticated power of attorney and the required identity documents. The Amharic text above is the authoritative version.