Shareholder Notice · የባለአክሲዮኖች ማስታወቂያ

General Assembly.

5th Ordinary Session
Sene 23, 2018 E.C. · 30 June 2026
All announcements
የኒኦ አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም አ.ማ
የባለአክሲዮኖች 5ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ
የጉባኤ ጥሪ

በኢትዮጵያ የንግድ ሕግ አዋጅ ቁጥር 1243/2013 አንቀጽ 366 (1)፤ 367 (1)፤ 370 እና 393 እንዲሁም በተቋሙ መመስረቻ ጽሑፍ አንቀጽ አስራ ስምንት (1) መሰረት የኒኦ አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም አ.ማ የባለአክሲዮኖች 5ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ የሚከተለውን ጊዜ በተቋሙ ዋና መ/ቤት በሚገኘው የመሰብሰቢያ አዳራሽ ውስጥ ያካሂዳል፡፡ በመሆኑም የተከበራችሁ የተቋሙ ባለአክሲዮኖች በዕለቱ በጉባኤው ላይ እንድትገኙልን የተቋሙ የዳይሬክተሮች ቦርድ በአክብሮት ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡

ማክሰኞ ሰኔ 23 ቀን 2018 ዓ.ም · ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ጀምሮ
Tuesday, Sene 23, 2018 E.C. (30 June 2026) · from 9:00 AM · Institution head office, meeting hall
1. አክሲዮን ማህበሩን የሚመለከቱ ዋና ዋና መረጃዎች
ዋና መ/ቤት አድራሻ · Head office
አዲስ አበባ · ቂርቆስ ክ/ከተማ · ወረዳ 8 · ንጉስት ታወር
ድህረ ገጽ · Website
neo.et
የምዝገባ ቁጥር · Registration No.
MT/AA/3/0053054/2014
የማህበሩ ስም · Company name
ኒኦ አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም አ.ማ
የማህበሩ አይነት · Type
በማይክሮፋይናንስ ስራ የተሰማራ
የተፈረመ ካፒታል · Subscribed capital
ብር 160,649,000.00
የተከፈለ ካፒታል · Paid-up capital
ብር 160,649,000.00
2. የ5ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ አጀንዳዎች
  1. የጉባኤውን አጀንዳዎች ማጽደቅ፤
  2. በማህበሩ ከተፈረሙ አክሲዮኖች መካከል በ2024/2025 በጀት ዓመት መከፈል ያለባቸው ለነባር ባለአክሲዮኖች የተከፋፈሉ አዳዲስ አክሲዮኖች ሙሉ በሙሉ በጥሬ ገንዘብ መከፈላቸውን ሪፖርት መስማት እና ተወያይቶ መወሰን፤
  3. በ2024/2025 በጀት ዓመት በተገኘው የተጣራ ትርፍ አደላደል እና ወደ ተከፈለ ካፒታል እንዲያድግ ተወያይቶ መወሰን፤
  4. የጉባኤውን ቃለ ጉባኤ ማጽደቅ፡፡
3. ማሳሰቢያ
  1. ባለአክሲዮኖች ለስብሰባ በሚመጡበት ጊዜ ማንነትን የሚያረጋግጥ የታደሰ የቀበሌ የነዋሪነት መታወቂያ፤ የፋይዳ መታወቂያ፤ ፓስፖርት ወይንም መንጃ ፍቃድ — ዋናውን እና ቅጂውን ይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል፤
  2. በጉባኤው ላይ በአካል የማይገኙ ባለአክሲዮኖች በንግድ ሕግ አንቀጽ 373 መሰረት በወኪሎቻቸው አማካይነት መሳተፍ የሚችሉ ሲሆን፤ ውል ለማዋዋል ስልጣን በተሰጠው አካል የተረጋገጠ የውክልና ማስረጃ በመያዝ በተወካይ አማካይነት በጉባኤው ላይ መሳተፍ ይችላሉ፤
  3. በባለአክሲዮኖች የተሰጠ ወይም ውል ለማዋዋል ስልጣን በተሰጠው አካል የተረጋገጠ ማስረጃ የያዛችሁ ተወካዮች፤
    1. ማንነትን የሚያሳይ የታደሰ የቀበሌ መታወቂያ፤ የፋይዳ መታወቂያ፤ ፓስፖርት ወይም መንጃ ፍቃድ — ዋናውን እና ቅጂውን፤
    2. የወኪሉን የታደሰ የቀበሌ መታወቂያ፤ የፋይዳ መታወቂያ፤ ፓስፖርት ወይም መንጃ ፍቃድ ቅጂ እንዲሁም፤
    3. በጉባኤው ለመሳተፍ እና ድምጽ ለመስጠት የሚያስችል የውክልና ስልጣን ማስረጃ — ዋናውን እና ቅጂውን ይዛችሁ በመቅረብ በጉባኤው ላይ መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን በአክብሮት እናሳውቃለን፡፡
ኒኦ አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም አ.ማ
የዳይሬክተሮች ቦርድ

In brief (English): The Board of Directors of Neo Microfinance Institution S.C. convenes the 5th Ordinary General Assembly of Shareholders on Tuesday, Sene 23, 2018 E.C. (30 June 2026) from 9:00 AM at the head office, under Commercial Code Proclamation No. 1243/2013. Agenda: adopt the agenda; receive and decide on the report that new shares allotted to existing shareholders for FY 2024/25 were paid in full in cash; decide on allocation of FY 2024/25 net profit and its capitalisation; approve the minutes. Attending shareholders must bring the original and a copy of a valid ID (Kebele residence ID, Fayda, passport, or driving licence); proxies may attend under Article 373 with an authenticated power of attorney and the required identity documents. The Amharic text above is the authoritative version.